ARTICLES




THE BREAD OF LIFE
ለሰው ሁሉ በፍቅር የምናካፍለው የዘለዓለም ሕይወት እንጀራ:
ሰላም! ሰላም!! ሰላም!!!
እስቲ ስለክርስትና በመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ላይ ተመርኩዤ ትንሽ የገባኝን ላካፍል:
1) አዳም አትብላ የተባለውን በልቶ/ኃጢአት/ ከፍጣሪው ጋር ተጣላ/ተለየ ወይም ከገነት ወጣ! (ዘፍጥረት 3 በሙሉ, ሮሜ 3:11-18 እና 23)
2) የኃጢያት ደሞዝ/ክፍያ ሞት ነው (ሮሜ6:23 ደም ካልፈሰሰ ደግሞ የኃጢአት ስርየት የለም (እብራውያን 9:22-23)
3) ጥያቄው ከዚህ ባለመታዘዝ ከመጣብን ሞት እንዴት መዳን ይቻላል? ነው!
ይህን ጥያቄ ታላላቅ ነቢያትና ሐዋርያት ( ማንም ሰው) እንዲሁም ፍጡር የሆኑት መላእክትም ሊመልሱት ስለማይችሉት እግዚአብሔር በመዝሙር (49):7 ላይ ''ወንድም ወንድሙን አያድንም ሰውም አያድንም'' አለ!
በዚህ መሰረት:
ሀ) ነቢዩ ኢሳያስ በ 7:14 ላይ ''ድንግል ትጸንሳለች....'' በ59:16 ላይ ደግሞ ''ሰውም እንደሌለ አየ .... ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድሃኒት አመጣለት! ጽድቁም አገዘው''
ለ) በማቴዎስ 1:21 ላይ ''እርሱ/ ከማርያም የተወለደው/ ሕዝቡን ከሐጢአታቸው ያድናቸዋልና''
ሐ) በዮሐንስ 3:16 ላይ ''በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና''
መ) በሐዋርያት ሥራ 4:12 ላይ ''መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና'' በማለት ሲያጠቃልለው
ሠ) በ1ኛ ዮሐንስ 1: 7-10 ላይ ''.....የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻል..... ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርግዋለን (እግዚርን) ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም''
በማለት ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራእይ ያሉት 66ቱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት ስለክርስትና ዋና ዓላማ በማያሻማ መልኩ ሰፍሯል!
ስለዚህ ክርስትና ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቶ ከገነት የወጣውን የሰው/የአዳም ዘር በሙሉ በክርስቶስ ሰው ሆኖ በመምጣት በእኛ በኃጢያተኞች ፋንታ በመሰቀልና በመሞት ከተያዝንበት የሞት እጅ በደሙ ዋጋ በመግዛት ከዚያም በመቀበርና በመነሳት ሕይወትን ሰጠን!በመጨረሻም ወደ አባቱ አርጎ ቤት ካዘጋጀልን በሗላ ተመልሶ በመምጣት ቤተ ክርስቲያንን (እንደቃሉ በእሱ ያመኑትን) እንደሚወስድ ተናግሮና አማኞች እሱ የጀመረውን ሥራ እንዲፈጽሙት የሚያስችላቸውን ቅዱሱን መንፈስ እንደሚልክላቸው ቃል ገብቶ ከላይ እንደ ወረደ ወደዚያው በመውጣት የተናገረውን ሦሥተኛ የመለኮት አካል እናቱን ማርያምን ጨምሮ በ120 ሰዎች ላይ በጴንቴ ኮስት (Pentecost) ቀን ለቀቀው!!!
በዚህ መሰረት ክርስትና ማለት ይህን አውቆና አምኖ በተግባር(ዮሐ 13:17) በሰላምና በፍቅር የሚኖር የደስታ ሕይወት ነው እንጂ ሰው ሠራሽ ሃይማኖት አይደለምና ይህን እውነት ከሚቀርቡን ታማኝ ቤተ ሰቦቻችንና ጉዋደኞቻችን ጋር መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ቤርያ ሰዎች በልበ ሰፊነት (ሥራ17:11-12) በማንበብ ነፍሳችን እረፍትን እንድታገኝ በግላችን ዛሬውኑ እንድንወስን ከልቤ እመክራለሁ!!!
ከዚህ በተረፈ ማዎቅ ያለብን ነገር ቢኖር በመስቀል ላይ በተሠራ ሥራ እንጂ በሌላ ልፋት መንግሥተ ሰማይ ለመግባት መሞከር የጌታን ሞትና ትንሳኤን ከንቱ ለማድረግ መሞከርና እንዳልተደረገልን መቁጠር ነው!!!
ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን!
አሜን!!!

Comments

Popular posts from this blog