ARTICLES
If don't mind please share the following TRUTH of LIFE to your family & friends:
ሰላም! ሰላም!! ሰላም!!!
እስቲ ስለክርስትና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ላይ ተመርኩዤ ትንሽ የገባኝን ላካፍል:
1) አዳም አትብላ የተባለውን በልቶ/ኃጢአት/ ከፍጣሪው ጋር ተጣላ/ተለየ ወይም ከገነት ወጣ! (ዘፍጥረት 3 በሙሉ, ሮሜ 3:11-18 እና 23)
2) የኃጢያት ደሞዝ/ክፍያ ሞት ነው (ሮሜ6:23 ደም ካልፈሰሰ ደግሞ የኃጢአት ስርየት የለም (እብራውያን 9:22-23)
3) ጥያቄው ከዚህ ባለመታዘዝ ከመጣብን ሞት እንዴት መዳን ይቻላል? ነው!
ይህን ጥያቄ ታላላቅ ነቢያትና ሐዋርያት ( ማንም ሰው) እንዲሁም ፍጡር የሆኑት መላእክትም ሊመልሱት ስለማይችሉ እግዚአብሔር በመዝሙር (49):7 ላይ ''ወንድም ወንድሙን አያድንም ሰውም አያድንም'' አለ! በዚህ መሰረት:
ሀ) ነቢዩ ኢሳያስ በ 7:14 ላይ ''ድንግል ትጸንሳለች....'' በ59:16 ላይ ደግሞ ''ሰውም እንደሌለ አየ .... ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድሃኒት አመጣለት! ጽድቁም አገዘው''
ለ) በማቴዎስ 1:21 ላይ ''እርሱ/ ከማርያም የተወለደው/ ሕዝቡን ከሐጢአታቸው ያድናቸዋልና'' ሐ) በዮሐንስ 3:16 ላይ ''በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና''
መ) በሐዋርያት ሥራ 4:12 ላይ ''መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና'' በማለት ሲያጠቃልለው
ሠ) በ1ኛ ዮሐንስ 1: 7-10 ላይ ''.....የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻል..... ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርግዋለን (እግዚርን) ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም''
በማለት ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራእይ ያሉትን 66 የመጽሐፍ ቅዱስን መጽሐፍት ስለክርስትና ዋና ዓላማ ባጭሩ ያስቀምጠዋል!!! ስለዚህ ክርስትና ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቶ ከገነት የወጣውን የሰው/የአዳም ዘር በክርስቶስ ሰው ሆኖ በመምጣት, በመስቀል ላይ በመሞት, በመቀበር, በመነሳትና በማረግ! በመጨረሻም እንደሚመጣ አምኖ በተግባር የሰላምና የፍቅር ሕይወት የሚኖር ነው እንጂ ሌላ ሰው ሠራሽ ሃይማኖት አይደለምና ይህን በጥሞና ከሚቀርቡን ታማኝ የመጸሐፍ ቅዱስ ሰዎች ጋር ተወያይተን አቋም ለራስ እንድንይዝ ከልቤ እመክራለሁ!!!
በመስቀል ላይ በተሠራ ሥራ እንጂ በሌላ ልፋት መንግሥተ ሰማይ ለመግባት መሞከር የጌታን ሞትና ትንሳኤን ከንቱ ማድረግ ነው!!!
ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን!
አሜን!!!
Comments
Post a Comment