ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል
ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል!
መጽሐፈ ምሳሌ 29:23
"ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ መንፈሱን የሚያዋርድ ግን ክብርን ይቀበላል።"
ኩራት ወይም ትዕቢት ተጽዕኖም አለው:: ለምሳሌ አንድ ሰው ቅር አስኝቶን ይሆናል ነገር ግን የእኛ ኩራት ወይም ትዕቢት ይቅርታ እንዳንጠይቅ ያደርገናል:: የተበላሽውን ግንኙነት ማስተካከል እንዳለብን ልንገነዘብ እንችላለን, ነገር ግን ትዕቢት ይህን ፍላጎት እንድንክድ ያደርገናል::
መንፈስ ቅዱስ ለውስጣችን የሚመስክርልን ልናስተካክለው የሚገባ ነገር ሊኖር ይችላል: ነገር ግን ትዕቢት የእኛን ስሜት መቀበል ይከብደዋል::
ትዕቢት ሕክምና ያስፈልገዋል:: ትዕቢት ሌሎችን ማገልገልን አይችልም. ከዚህ ይልቅ ትዕቢት ታዋቂ ቦታዎችን ለማግኘት ይጥራል:: ትዕቢት እውነተኛ የሆኑ አማካሪዎችን ችላ ይላል:: ትዕቢተኛ ተጠያቂ መሆንንም: አይፈልግም::
በሌላ በኩል ደግሞ ትሕትና: እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ከመሆኑም በላይ ሕይወታችንን አምላክ በሚያስከብር ቦታ ላይ ያስቀምጣል:: ትዕቢትን ሕይወታችንን ከማጥፋቱ በፊት በእሱ ላይ ድል እንዲስጠን ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ.
Comments
Post a Comment