Popular posts from this blog
ARTICLES
THE BREAD OF LIFE ለሰው ሁሉ በፍቅር የምናካፍለው የዘለዓለም ሕይወት እንጀራ: ሰላም! ሰላም!! ሰላም!!! እስቲ ስለክርስትና በመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ላይ ተመርኩዤ ትንሽ የገባኝን ላካፍል: 1) አዳም አትብላ የተባለውን በልቶ/ኃጢአት/ ከፍጣሪው ጋር ተጣላ/ተለየ ወይም ከገነት ወጣ! (ዘፍጥረት 3 በሙሉ, ሮሜ 3:11-18 እና 23) 2) የኃጢያት ደሞዝ/ክፍያ ሞት ነው (ሮሜ6:23 ደም ካልፈሰሰ ደግሞ የኃጢአት ስርየት የለም (እብራውያን 9:22-23) 3) ጥያቄው ከዚህ ባለመታዘዝ ከመጣብን ሞት እንዴት መዳን ይቻላል? ነው! ይህን ጥያቄ ታላላቅ ነቢያትና ሐዋርያት ( ማንም ሰው) እንዲሁም ፍጡር የሆኑት መላእክትም ሊመልሱት ስለማይችሉት እግዚአብሔር በመዝሙር (49):7 ላይ ''ወንድም ወንድሙን አያድንም ሰውም አያድንም'' አለ! በዚህ መሰረት: ሀ) ነቢዩ ኢሳያስ በ 7:14 ላይ ''ድንግል ትጸንሳለች....'' በ59:16 ላይ ደግሞ ''ሰውም እንደሌለ አየ .... ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድሃኒት አመጣለት! ጽድቁም አገዘው'' ለ) በማቴዎስ 1:21 ላይ ''እርሱ/ ከማርያም የተወለደው/ ሕዝቡን ከሐጢአታቸው ያድናቸዋልና'' ሐ) በዮሐንስ 3:16 ላይ ''በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና'' መ) በሐዋርያት ሥራ 4:12 ላይ ''መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና'' በማለት ሲያጠቃልለው ሠ) በ1ኛ...
አቶ ሀብታሙ(ይዲዲያ) ጳውሎስ፤ የቀደሙ አባቶችን መስማት፣ ከእነሱ መማርና እነሱንም መምሰል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑ ባይገለጥልህ አያስደንቅም፡፡ ምክንያቱም ስለማንነታችሁ ክርስቶስ እራሱ አስረግጦ ተናግሯልና፡፡ ለመሆኑ ለብርና ወርቅ ብሎ ወንጌልን የሚሸቅጠው ማን እንደሆነ ለእግዚአብሔር አምላክ የተሰወረ ይሆን? ተሰውሮ ሳይሆን እርሱ መሀሪና ይቅር ባይ አምላክ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን ከርስቶስን እራሱን ስንት ጊዜ እንደፈተነው አንዘነጋም፡፡ በእናንተም በእነ አቶ ሀብታሙ (ይዲዲያ) የሚሰራ የሚመስለው ሰይጣን በስጋ ያከበራችሁና ያበለፀጋችሁ መስሏችሁ የዘላለም ሕይወታችሁን እንዳታጡ ንሥሀስ ብትገቡ መሀሪ አምላክ ነውና ይቅር ይላችኋል፡፡ ይህን ምስኪን ሕዝብም እባካችሁ በሥጋ በተለያየ መከራ ውስጥ መኖሩ አንሶ ቢያንስ የዘላለም ህይወቱን እንዲያጣ ባታደርጉት እጅግ ደስ ይለኛል፡፡ አምላክም በዚህ ደስ ይለዋል፡፡ ጌታ ሆይ ፣ ጌታ ሆይ የሚሉ …መንግስተ ሰማያትን አይወርሱም…አረ ስንቱን ልጥቀስ….እርሱ ይቅር ይበልህ ይበላችሁ!!
ReplyDelete