Popular posts from this blog
ARTICLES
THE BREAD OF LIFE ለሰው ሁሉ በፍቅር የምናካፍለው የዘለዓለም ሕይወት እንጀራ: ሰላም! ሰላም!! ሰላም!!! እስቲ ስለክርስትና በመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ላይ ተመርኩዤ ትንሽ የገባኝን ላካፍል: 1) አዳም አትብላ የተባለውን በልቶ/ኃጢአት/ ከፍጣሪው ጋር ተጣላ/ተለየ ወይም ከገነት ወጣ! (ዘፍጥረት 3 በሙሉ, ሮሜ 3:11-18 እና 23) 2) የኃጢያት ደሞዝ/ክፍያ ሞት ነው (ሮሜ6:23 ደም ካልፈሰሰ ደግሞ የኃጢአት ስርየት የለም (እብራውያን 9:22-23) 3) ጥያቄው ከዚህ ባለመታዘዝ ከመጣብን ሞት እንዴት መዳን ይቻላል? ነው! ይህን ጥያቄ ታላላቅ ነቢያትና ሐዋርያት ( ማንም ሰው) እንዲሁም ፍጡር የሆኑት መላእክትም ሊመልሱት ስለማይችሉት እግዚአብሔር በመዝሙር (49):7 ላይ ''ወንድም ወንድሙን አያድንም ሰውም አያድንም'' አለ! በዚህ መሰረት: ሀ) ነቢዩ ኢሳያስ በ 7:14 ላይ ''ድንግል ትጸንሳለች....'' በ59:16 ላይ ደግሞ ''ሰውም እንደሌለ አየ .... ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድሃኒት አመጣለት! ጽድቁም አገዘው'' ለ) በማቴዎስ 1:21 ላይ ''እርሱ/ ከማርያም የተወለደው/ ሕዝቡን ከሐጢአታቸው ያድናቸዋልና'' ሐ) በዮሐንስ 3:16 ላይ ''በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና'' መ) በሐዋርያት ሥራ 4:12 ላይ ''መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና'' በማለት ሲያጠቃልለው ሠ) በ1ኛ...
ፕሬዝደንቱ 400 የአጸድ ነብያትና 450 የበዓል ነብያት እኔ እስክማውቀው 950 ነው ብለው በኣማርኛና በእንግሊዘኛ ሲሳሳቱ ምን እንበላቸው... በዚህ የሂሳብ ስሌት ስህተት ሁል ግዜም የሚናገሩት ስህተት ነው እንበልን?
ReplyDeleteበመፀሐፍ ቅዱስ ነብያት በራሳቸው አስትያየት ስህተት ሊናገሩ ይችላሉ ደግሞም የታረማሉ ነገር ግን ሃሰተኛ ነቢይ አይባሉም።
ነብዩ ሳሙኤል በራሱ አስተያየት እግዚአብሔር የቀባው ኤልያብን ነው ብሎ ተሳስቶ ነበር፣ ነገር ግን ወዲያው እግዚአብሔር አእስተካከለው ። ነብዪ ሳሚኤል በኤልያብ ላይ የተነበየው ስህተት መሆኑ ግልፅ ቢሆንም ሳሙኤል ግን ሃሰተኛ ነብይ ግን ተብሎ አያውቅም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ወዲያው ስላስተካከለው።
ስለዚህ ስህተቶች ሲኖሩ መጅመሪያ ለማስተካከል መሞከር እንጂ በመግለጫ የምታወርዱት የጡጫና የዱላው ናዳ ባይቀድም መልካም ነው። ፍቅር ከሁሉ ይበልጣል!
ጌታ በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጠን!!